Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ጨፌ ኦሮሚያ 5ኛ መጀበኛ ጉባዔውን ነገ ማካሄድ ይጀምራል

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ለሁለት ቀናት የሚቆየው የጨፌ ኦሮሚያ 6ኛ የስራ ዘመን፣ 2ኛ ዓመት 5ኛ መደበኛ ጉባዔ ነገ በአዳማ ከተማ መካሄድ ይጀምራል።

ጉባዔውን አስመልክቶ የጨፌ ኦሮሚያ አፈ ጉባዔ ወ/ሮ ሰዓዳ አብዱራህማን መግለጫ ሰጥተዋል።

አፈ ጉባዔዋ በመግለጫቸው÷በጉባዔው የተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ውይይት ተደርጎ ውሳኔዎች ይተላለፋሉ ብለዋል።

የበጀት ዓመቱ የክልሉ መንግስት አፈፃፀም ሪፖርት እና ቀጣይ ዕቅድ ቀርቦ ውይይት እንደሚደረግበትም ነው የገለጹት ።

የበጀት አጠቃቀም፣ የሰላም እና የፀጥታ ጉዳይ፣ የዜግነት አገልግሎት፣ የልማት ስራዎች እና የህዝቡ ተደጋጋሚ ጥያቄ የሆነው የመልካም አስተዳደር እንዲሁም የአገልግሎት አሰጣጥ ቀዳሚ የውይይት ርዕሶች እንደሚሆኑም ተገልጿል፡፡

በተጨማሪም ጉባዔው በሁለት ቀናት ቆይታው ሁለት ረቂቅ አዋጆችን ተወያይቶ ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል።

ረቂቅ አዋጆችም÷የ2015 ዓ/ም የበጀት ዓመት ተጨማሪ በጀት እና የ2016 ዓ/ም በጀት ዓመት ረቂቅ አዋጆች መሆናቸውን በመግለጫው ተጠቅሷል፡፡

በመራኦል ከድር

Exit mobile version