Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የአዲስ አበባ ከተማ የ2016 በጀት 140 ነጥብ 29 ቢሊየን ብር ሆኖ ጸደቀ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2016 ዓ.ም በጀት 140 ነጥብ 29 ቢሊየን ብር ሆኖ ጸደቀ፡፡

የከተማዋ ምክር ቤት የከተማ አስተዳደሩን የ2016 ዓ.ም በጀት አመት 140 ነጥብ 29 ቢሊየን ብር በጀት በአብላጫ ድምፅ አፅድቋል፡፡

ከቀረበው በጀት 23 ቢሊየን 498 ሚሊየን 446 ሺህ 197 ብር ለመደበኛ ወጪ፣ 69 ቢሊየን 336 ሚሊየን 835 ሺህ 72 ብር ለካፒታል ወጪ እንዲሁም ለመጠባበቂያ በጀት 5 ቢሊየን 300 ሚሊየን ብር በጀት እንደተያዘ ተጠቅሷል፡፡

በተጨማሪም ለክፍለ ከተሞች መደበኛ በጀት ወጪ 33 ቢሊየን 498 ሚሊየን 495 ሺህ 1 ብር፣ ለካፒታል ወጪ 8 ቢሊየን 657 ሚሊየን 773 ሺህ 794 ብር ተመድቧል ተብሏል፡፡

በጥቅሉ ምክር ቤቱ ለአስተዳደሩ የ140 ቢሊየን 291 ሚሊየን 550 ሺህ 64 ብር በጀት ለመደበኛ፣ ካፒታልና መጠባበቂያ በጀት በማፅደቅ ጉባዔውን እንዳጠናቀቀ የከተማ አስተዳደሩ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

Exit mobile version