አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል የ2015/16 ምርት ዘመን የሩዝ ክላስተር ዘር ማስጀመሪያ መርሐ ግብር በደቡብ ጎንደር ዞን ሊቦ ከምከም ወረዳ እየተካሄደ ነው፡፡
ሩዝ ሰብልን በማስፋፋት ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥም እንዲሁም ለገበያ በማቅረብ የሕዝቡን ተጠቃሚነት ለማስፋት የክልሉ ግብርና ቢሮ ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ መሆኑ ተገልጿል፡፡
በሊቦ ከምከም ወረዳ ቡራ ቀበሌ ብቻ 482 ሔክታር መሬት በክላስተር እንደሚለማ መጠቆሙን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡