አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 24 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) 1 ሺህ 351 አሽከርካሪዎች ከተፈቀደላቸው ተራ ቀን ውጭ ሲያሽከረክሩ በመገኘታቸው አስፈላጊው እርምጃ እንደተወሰደባቸው የአዲስ አበባ ከተማ ፓሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅን ለማስፈፀም የወጣውን የትራንስፖርት ዘርፍ አፈፃፀም መመሪያ ተከትሎ በተደረገ ቁጥጥር ከተፈቀደላቸው ቀን ውጭ ሲንቀሳቀሱ በተገኙ ኮድ 2 አሸከርካሪዎች ላይ እርምጃ መወሰዱን በኮሚሽኑ የትራፊክ ቁጥጥር መምሪያ የቀጠና ኃላፊ ኮማንደር በኃይሉ ደጀኔ ተናግረዋል።
በሰሌዳ ተራቸው መሰረት በማይንቀሳቀሱ አሽከርካሪዎች ላይ የሚወሰደው እርምጃ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል።
በተመሳሳይ የኮቪዲ-19 ወረርሽኙን ለመከላከል ለመቆጣጠርና የሚያስከትለውን ጉዳት ለመቀነስ የወጣውን የአስቸኮይ ጊዜ አዋጅ ክልከላን በመተላለፍ በትራንስፖርት አሽከርካሪዎች ላይ በተደረገው ቁጥጥር ከተፈቀደው የተሳፋሪ ቁጥር በላይ ጭነው የተገኙ 392 እና ከታርፍ በላይ ሲያስከፍሉ በተገኙ 292 አሽከርካሪዎችም ላይ እርምጃ መወሰዱን ኃላፊው አብራርተዋል፡፡

