Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ከንቲባ አዳነች ከፌዴራል መንግስት ከፍተኛ አመራሮች የሱፐርቪዢን ቡድን ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከፌዴራል መንግስት ከፍተኛ አመራሮች የሱፐርቪዢን ቡድን ጋር ተወያዩ፡፡

ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ እንደገለጹት÷የከተማ አስተዳደሩን የክረምት ስራዎች አፈፃፀም ለመመልከት እና ለመደገፍ ከፌዴራል መንግስት ከፍተኛ አመራሮች የሱፐርቪዢን ቡድን ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡

ቡድኑ ለተከታታይ 10 ቀናት በክፍለ ከተሞች እና ወረዳዎች የሱፐርቪዢን ስራ የሚያካሂድ ይሆናልም ብለዋል።

በከተማዋ ለዓመታት የተከማቹ ችግሮችን መፍታት ከፍተኛ ጥረት እና በርካታ ትብብርን የሚጠይቅ በመሆኑ
የፌደራል መንግስት ክትትልና ድጋፍ ማድረጉ ተገቢ እንደሆነም ገልጸዋል፡፡

አዲስ አበባን እንደስሟ ውብ፤ ለኑሮና ለስራ ምቹ ከተማ ለማድረግ በትጋት መስራታችንን እንቀጥላለን ሲሉም መልዕክታቸውን አስተለልፈዋል፡

Exit mobile version