Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በኢንጂነር አይሻ የተመራው ቡድን በጌዴኦ የሥራ አፈጻጸም እየተመለከተ ነው

 

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢፌዲሪ መስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሐመድ የተመራ የሚኒስትሮች ቡድን በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ጌዴኦ ዞን በመገኘት የተመረጡ የከተማና የገጠር ተግባራት አፈጻጸም የሚገኝበትን ደረጃ እየተመለከተ ነው፡፡

ከዞኑ አመራሮች ጋር ዉይይት በማድረግ የሱፐርዥን ስራውን የጀመረዉ የሚኒስትሮች ቡድን ከሥራ ዕድሎች ፈጠራ፣ ከበጎ ፈቃድ አገልግሎት፣ ከአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ-ግብር፣ ከሌማት ትሩፋት፣ የግብርና ምርትና ምርታማነትን ከማሳደግና አንጻር እና ከመሣሰሉት ጉዳዮች አኳያ እየተከናወኑ ያሉ ሥራዎችን ተንቀሳቅሶ መመልከት ጀምሯል።

ቡድኑ ቀደም ሲል ከደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል ከፍተኛ አመራሮች ጋር በተልዕኮዉ ዙሪያ ሠኔ 30 እና ሐምሌ 1 ቀን 2015 ተወያይቶ ወደ ሥራ መግባቱን ከጌዴኦ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

Exit mobile version