Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ገቢው የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የሚውል ንጋት የተሰኘ የሙዚቃ አልበም ተመረቀ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 24 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ገቢው የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የሚውል ንጋት የተሰኘ የሙዚቃ አልበም ተመረቀ።

የሙዚቃ አልበሙ ከኢትዮጵያ የሙዚቃ ዘርፎች ማህበራት ህብረት ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ተበርክቷል።

በአልበሙ ላይ ዘሪቱ ከበደ፣ሄኖክ መሀሪ፣ጆኒ ራጋ፣ቤቲ ጂና ፍቅረአዲስ ነቃጥበብን ጨምሮ 15 ድምፃውያን ተሳትፈውበታል።

ከአልበሙ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የሚደረገውን ጥረት ለመደገፍ እንደሚውል ከከንቲባ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

Exit mobile version