Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በአንድ ጀንበር 500 ሚሊየን ችግኞችን ለመትከል 361 ሺህ 415 ሄክታር መሬት ተዘጋጅቷል – ሚኒስቴሩ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)በኢትዮጰያ በአንድ ጀንበር 500 ሚሊየን ችግኞችን ለመትከል ለተያዘው እቅድ 361 ሺህ 415 ሄክታር መሬት መዘጋጀቱን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ።

በሚኒስቴሩ የተፈጠሮ ሀብት ልማት ሚኒስትር ዴኤታ ፕሮፌሰር እያሱ ኤልያስ÷በአንድ ጀንበር ለሚካሄደው የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር 9 ሺህ 500 የመትከያ አካባቢዎች መለየታቸውን ገልጸዋል።

ለ500 ሚሊየን ችግኞች መትከያ 361 ሺህ 415 ሄክታር መሬት መዘጋጀቱንም ሚኒስትር ዴታው ተናግረዋል።

በዕለቱ በየአካባቢው የሚደረጉ የችግኝ ተከላዎችን ከስፍራው በቀጥታ ለዓለም ህዝብ ተደራሽ ለማድረግ የካርታና GREENLEGACY.ET የዌብ ዝግጅት መደረጉንም ጠቁመዋል።

ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርና ከስፔስ ሳይንስ ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር 9 ሺህ 500 ቦታዎችን በካርታ የማካተትና ድረገፅ በማበልፀግ ወደ ስራ መገባቱን ፕሮፌሰር እያሱ ተናግረዋል።

በእለቱ ከ25 ሚሊየን በላይ ህዝብ በችግኝ ተከላው እንደሚሳተፍ ጠቅሰው ዜጎች ሁሉ በነቂስ ወጥተው አሻራቸውን እንዲያኖሩ ሚኒስትር ዴታው ጥሪ ማቅረባቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ሐምሌ 10 ቀን 2015 ዓ.ም በአንድ ጀንበር 500 ሚሊየን ችግኞችን ለመትከል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)ጥሪ ማድረጋቸው ይታወቃል፡፡

Exit mobile version