Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በአማራ ክልል በአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር 260 ሚሊየን ችግኞች ይተከላሉ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል በአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር 260 ሚሊየን ችግኞች እንደሚተከሉ የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ።

የቢሮው ምክትል ሃላፊ አልማዝ ጊዜው (ዶ/ር) ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንዳሉት÷ የፊታችን ሐምሌ 10 ቀን 2015 ዓ.ም በአንድ ጀምበር 260 ሚሊየን ችግኞችን ለመትከል አስፈላጊውን ዝግጅት ተደርጓል።

ለችግኝ ተከላ መርሐ ግብሩም 26 ሺህ ሄክታር መሬት መዘጋጀቱን ነው የተናገሩት፡፡

በዕለቱ በየአካባቢው የሚደረጉ የችግኝ ተከላዎችን ከስፍራው በቀጥታ ለዓለም ሕዝብ ተደራሽ ለማድረግ የካርታ እና የዌብ ዝግጅት ተደርጓልም ነው ያሉት፡፡

የመትከያ ቦታዎች በካርታ የማካተትና ድረገፅ በማበልፀግ ስራ መጠናቀቁንም ምክትል ሃላፊዋ ተናግረዋል፡፡

በዕለቱ ከ5 ሚሊየን በላይ ሕዝብ በችግኝ ተከላ መርሐ ግብሩ እንደሚሳተፍም ጠቁመዋል፡፡

በአማራ ክልል ለዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር 1 ነጥብ 65 ቢሊየን ችግኝ መዘጋጀቱን የቢሮው መረጃ ያመላክታል፡፡

 

Exit mobile version