Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ሸበሌ ባንክ በጅግጅጋ በእሳት አደጋ ንብረታቸውን ላጡ ነጋዴዎች የ20 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ሸበሌ ባንክ በጅግጅጋ ገበያ ማዕከል በተከሰተው የእሳት አደጋ ንብረታቸውን ላጡ ነጋዴዎች የ20 ሚሊየን ብር ድጋፍ አድርጓል፡፡

ድጋፉን የሸበሌ ባንክ ዋና ዳይሬክተር አቶ ከድር አህመድ ከባንኩ አመራሮች ጋር በመሆን ለክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሃመድ አስረክበዋል።

የተደረገው ድጋፍ በአደጋው ጉዳት የደረሰባቸው ነጋዴዎችን ለመደገፍና ለማቋቋም የሚደረገውን ጥረት እንደሚያግዝ ተጠቁሟል፡፡

በሌላ በኩል ረይስ ማይክሮ ፋይናንስ በጅግጅጋ የገበያ ማዕከል በተከሰተው የእሳት አደጋ ንብረታቸውን ላጡ ነጋዴዎች የ1 ሚሊየን ብር ድጋፍ ማድረጉን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

Exit mobile version