አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ-መንግስታት ድርጅት (ኢጋድ) ጥረት በቀጣናው መረጋጋት እንዲሰፍንና ሀገራቱ በልማት ሥራዎች እንዲዋሃዱ መሆኑን ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር)ገለጹ፡፡
የኢጋድ ዋና ጸሐፊ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) በለንደን “ቻትሃም” የዓለምአቀፍ ጉዳዮች እና ፖሊሲዎች ሐሳብ አመንጪ ኢኒስቲትዩት ተገኝተው ከቀጣናዊ እና ዓለምአቀፋዊ ዲፕሎማቶች ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይቸውም ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር)÷ ኢጋድ በሠራቸው ሥራዎች ስኬት ማስመዝገቡን አስረድተዋል፡፡
በቀጣናዊ ጉዳዮችም በውጣ ውረዶች ውስጥ ማለፉንም ነው ዋና ጸሐፊው በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው የገለጹት፡፡
ኢጋድ በዓለምአቀፋዊ ጉዳዮች እና ፖሊሲዎች ላይ ሐሳብ በማመንጨት በሚታወቀው “ቻትሃምኢኒስቲትዩት” ዘንድ ከፍተኛ ተቀባይነት እንዳለው በመመልከታቸውም ደስታ እንደተሰማቸው ገልጸዋል፡፡
ለድርጅቱ ስለሚያደርጉት ድጋፍም አመሥግነዋል፡፡