Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ለጉምሩክ ህጎች ተገዢ የሆነ ግብር ከፋይ መፍጠር ላይ በትኩረት ይሰራል-ወ/ሮ አይናለም ንጉሴ

 

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 6፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ስለታክስ በቂ ግንዛቤ ያለው እና ለታክስ እንዲሁም ለጉምሩክ ህጎች ተገዢ የሆነ ግብር ከፋይ መፍጠር በትኩረት የሚሰራበት ጉዳይ ነው ሲሉ የገቢዎች ሚኒስትር ወ/ሮ አይናለም ንጉሴ ተናገሩ፡፡

ሀገራዊ የታክስና ጉምሩክ ህግ ተገዢነት ንቅናቄ በአፋር ክልል ሰመራ ተጀምሯል፡፡

በመድረኩ የገቢዎች ሚኒስትር ወ/ሮ አይናለም ንጉሴ እንዳሉት÷ በህብረተሰቡ ዘንድ የታክስ ግንዛቤን ለማስፋት መሰል የንቅናቄ ሁነቶች ድርሻቸው የጎላ ነው፡፡

ስለታክስ በቂ ግንዛቤ ያለው እና ለታክስ እንዲሁም ለጉምሩክ ህጎች ተገዢ የሆነ ግብር ከፋይ መፍጠር በትኩረት የሚሰራበት ጉዳይ ነው ሲሉም ተናግረዋል፡፡

የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ በበኩላቸው÷ ግብር የሀገራችን ህልውና መሰረት እንደመሆኑ የሁላችንም ጉዳይ መሆን አለበት ማለታቸውን ከገቢዎች ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

Exit mobile version