አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 8፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በ13ኛው ዓመታዊ የአፍሪካውያን የስኬታማዎች ሽልማት (African Achievers Award) የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት (ኢጋድ) ዋና ፀሀፊ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) አሸናፊ ሆኑ።
ዋና ፀሀፊው ትናንት ምሽት በእንግሊዝ ለንደን በተካሄደ ስነ ስርዓት ላይ ተገኝተው ሽልማቱን ተቀብለዋል።
በትዊተር ገጻቸው ከሽልማቱ በኋላ ባስተላለፉት መልዕክትም ከዚህ ቀደም ሽልማቱን ከተቀበሉት ስኬታማ አፍሪካውያን ጋር በመሰለፋቸው የተሰማቸውን ክብር ገልጸዋል።
ለዚህ ክብር ለመብቃታቸው የኢጋድ ቤተሰቦችና ሌሎች በስራ ጉዟቸው ሁሉ ድጋፍ ያደረጉላቸው አካላት አስተዋጽኦ ከፍተኛ እንደሆነ አመላክተዋል።
በመተባበር ከተሰራ የአፍሪካን መጻዒ ጊዜ ብሩህ ማድረግ እንደሚቻልም መልዕክት አስተላልፈዋል።