Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

አብርሆት ቤተ-መጽሐፍት የሕግ ታራሚዎች በሥነ- ምግባር እንዲታነፁ ለማድረግ እየሠራ ነው

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 8፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አብርሆት ቤተ-መጽሐፍት የሕግ ታራሚዎች በሥነ- ምግባር እንዲታነፁ እና በዕውቀት እንዲበለጽጉ ለማገዝ ከቃሊቲ ፌደራል ማረሚያ ቤት ጋር በቋሚነት ሥራ መጀመሩን ገለጸ፡፡
የቤተ-መጽሐፍቱ ዳይሬክተር ውብአየሁ ማሞ (ኢ/ር) ከማረሚያ ቤቱ አስተዳደርና ከታራሚዎች ጋር ተወያይተዋል፡፡
ዳይሬክተሩ በውይይታቸው ላይ እንደገለጹት÷ የሕግ ታራሚዎች የፍርድ ጊዜያቸውን በንባብ እንዲያሳልፉ መሥራት ያስፈልጋል፡፡
ታራሚዎች በእርማት ጊዜያቸው እና ወደ ማሕበረሰቡ ሲቀላቀሉ አምራች ዜጋ ሆነው ከራሳቸው አልፈው ማሕበረሰቡን እንዲያገለግሉ ቤተ-መጽሐፉ ተነሳሽነቱን ወስዶ ከተለያዩ ማረሚያ ቤቶች ጋር እንደሚሰራ ገልጸዋል፡፡
ቤተ- መጽሐፉ ÷ ወቅታዊ፣ የሥነ- ልቦና፣ ሥነ- ምግባር፣ ሥነ- አዕምሮ፣ ሥነ ሰብ፣ ኪነ- ጥበብ፣ ፍልስፍና እንዲሁም የሣይንስ እና ቴክኖሎጂ መጽሐፍትን ጨምሮ ሌሎችንም ለታራሚዎች ተደራሽ ለማድረግ ይሠራል ተብሏል፡፡
የማረሚያ ቤቱ አስተዳደርና ታራሚዎች በበኩላቸው÷ አብርሆት ቤተ- መጽሐፍት የጀመረውን ሥራ በደስታ መቀበላቸውን እና አድናቆታቸውን ገልጸዋል፡፡
Exit mobile version