Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የአንድ ጀምበር የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር ተጀምሯል

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 10 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የአንድ ጀምበር የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር ተጀምሯል።
በክፍለ ከተማው የቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክን ጨምሮ በ12 ወረዳዎች በተመረጡ ቦታዎች የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር እየተከናወነ ይገኛል።
በክፍለ ከተማው ከ500 ሺህ በላይ ችግኞች በአንድ ጀምበር የሚተከሉ ሲሆን፥ ችግኞቹም ለከተማዋ ውበት የሚሆኑ፣ የፍራፍሬ፣ የጥላ ዛፎች ይገኙባቸዋል።
በመርሐ ግብሩ የተለያዩ ተቋማት፣ አመራሮች፣ የፀጥታ አካላት እና መላው ማህበረሰብ እየተሳተፈ ነው።
በሳሙኤል ወርቃየሁ
Exit mobile version