አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 10 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ችግኝ መትከላችንን በጠዋት ጀምረናል፣ እስከምሽት ይቀጥላል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ዛሬ ማለዳ ችግኝ በመትከል አሻራቸውን አኑረዋል።
በማለዳ በዝናብ ወጥታችሁ አረንጓዴ አሻራችሁን እያሳረፋችሁ ለምትገኙ ለመላው ኢትዮጵያውያን በሙሉ ምስጋናችን ይድረስ ብለዋል።
ዛሬ ኢትዮጵያውያን በህብረት ታሪክ የምንሰራበት ቀን ነው ያሉት ጠቅላይ ሚንስትሩ÷ ዛሬ ለእኛ ቀላል የሚመስለው ጉዳይ ብዙዎች የከበዳቸው እና የማይችሉት ነው ሲሉም ገልጸዋል።
ሕጻናት፣ አረጋውያን፣ አካል ጉዳተኞች፣ ሴቶች ሁሉም ኢትዮጵያውያን ሃገራቸውን አረንጓዴ አልብሰው ለመጭው ትውልድ ለማስተላለፍ መቁረጣቸው ትልቅ መታደል መሆኑንም ነው የተናገሩት።
በጠዋት ጀምረናል፤ እስከ ምሽት መትከላችን ይቀጥላል፣ በርቱ፣ በዝናብ የቆምነው የተሻለ ሀገር ለመፍጠር ነው ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።