Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ለአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር ስኬት ሁሉም ተሳትፎ ሊኖረው ይገባል- ጣሰው ወ/ሃና (ፕ/ር)

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 10፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር የቀጣዩ ትውልድ ዋስትና ስለሆነ ለስኬቱ የሁሉም ተሳትፎ ሊታከልበት እንደሚገባ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ጣሰው ወ/ሃና (ፕ/ር) ገለጹ፡፡

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አመራሮች እና ሠራተኞች በሀገር አቀፍ ደረጃ በአንድ ጀንበር 500 ሚሊየን ችግኝ የመትከል መርሐ ግብር ላይ ተሳትፈዋል፡፡

ጣሰው ወ/ሃና (ፕ/ር) በመርሐ ግብሩ ላይ እንደገለጹት÷ በዓየር ንብረት መዛባት የሚከሰትን ችግር በመከላከልና መቋቋም ረገድ የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር ሚና የጎላ ነው፡፡

መርሐ ግብሩ ለሀገር ዕድገት መሠረት ስለመሆኑም ነው ያመላከቱት፡፡

ለመርሐ ግብሩ ስኬትም አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከ1 ነጥብ 1 ሚሊየን በላይ ችግኞችን በማፍላት ለተለያዩ ተቋማት ድጋፍ ማድረጉን ገልጸዋል፡፡

Exit mobile version