Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የሥራ እና ክኅሎት ሚኒስቴር ከዓለም አቀፉ የሥራ ድርጅት ጋር በጋራ ለመስራት ተፈራረመ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሥራ እና ክኅሎት ሚኒስቴር ከዓለም አቀፉ የሥራ ድርጅት ጋር በክህሎት መር ምቹ ሥራ ዕድል ፈጠራና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ በጋራ መስራት የሚያስችለውን የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ፡፡

የሥራ እና ክኅሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ፥ ድርጅቱ በኢትዮጵያ ምቹና ዘላቂ የሥራ ዕድል ለመፍጠር የሚደረገውን ጥረት ሲደግፍ እንደቆየ አስታውቀዋል፡፡

አሁን የተፈረመው የመግባቢያ ሰነድም የሠራተኛ ፍልሰት አስተዳደርን ማሻሻል እንዲሁም ክህሎት መር የሥራ ዕድል ፈጠራን ማሳደግ እንደሚያስችል ጠቅሰዋል፡፡

በኢትዮጵያ፣ ጅቡቲ፣ ሶማሊያ፣ ሱዳንና ደቡብ ሱዳን የዓለም አቀፉ የሥራ ድርጅት ቢሮ ዳይሬክተርና የድርጅቱ የአፍሪካ ህብረት ልዩ ተወካይ አሌክሲዮ ሙሲንዶ በትብብር ለመስራት ላሳዩት ቁርጠኝነትና ተነሳሽነትም ሚኒስትሯ አመስግነዋል፡፡

Exit mobile version