Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

አምባሳደር ተሾመ ቶጋ ከዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት በኢትዮጵያ የፕሮግራሞች ሃላፊ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 12፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የብሄራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን ኮሚሽነር አምባሳደርተሾመ ቶጋ ከዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት በኢትዮጵያ የፕሮግራሞች ሃላፊ ኢምራህ ጉለር ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም የብሄራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን እና ዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት በትብብር መስራት በሚችሉበት ሁኔታ ላይ መክረዋል፡፡

በተለይም የቀድሞ ተዋጊዎችን መልሶ የማቋቋሙ ስራ በስኬት እንዲጠናቀቅ ተቋማቱ በቅንጅት መስራት በሚችሉበት አግባብ ላይ መወያየታቸውን አምባሳደር ተሾመ ቶጋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡

ዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት በኢትዮጵያ የብሄራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን አቅሙን እንዲያሳድግ በተለያዩ ዘርፎች ድጋፍ እያደረገ መሆኑም ተመላክቷል፡፡

Exit mobile version