Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ቻይና በራሷ መንገድ የአካባቢ ብክለትን ለመቀነስ ትሠራለች – ሺ ጂንፒንግ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 12፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ቻይና በራሷ መንገድ የአካባቢ ብክለትን ለመቀነስ እንደምትሠራ የሀገሪቷ ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ ገለጹ፡፡

ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ ይሄን ያሉት ÷ የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም ፈጣን እርምጃ እንዲወሰድ በጉዳዩ የአሜሪካ መልዕክተኛ የሆኑት ጆን ኬሪ ማሳሰባቸውን ተከትሎ ነው፡፡

የአሜሪካ የአየር ንብረት መልዕክተኛ ጆን ኬሪ ከቻይና ጠቅላይ ሚኒስትር ሊ ቺያንግ እና ከፍተኛ ዲፕሎማት ዋንግ ዪ ጋር መምከራቸውን ሲኤንኤን አስታውሶ ዘግቧል፡፡

በወቅቱም ጆን ኬሪ ቻይና የኃይሉን ዘርፍ ከበካይ ንጥረ ነገሮች እና ከሚቴን ጋዝ ነፃ ማድረግ አለባት ሲሉ አሳስበዋል፡፡

መልዕክተኛው ቻይና የደን ጭፍጨፋ መቀነስ አለባትም ብለው ነበር፡፡

ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ ÷ በተቀመጠው የልቀት ገደብ መሠረት ቻይና እስከ ፈረንጆቹ 2030 ድረስ የበካይ ጋዝ ልቀት መጠኗን ታስተካክላለች ብለዋል፡፡

በፈረንጆቹ 2060 ደግሞ በአየር ንብረት ላይ በካይ ጋዝ የማትለቅ ሀገር እንደምትሆን አረጋግጥላችኋለሁም ሲሉ ነው በቻይና እየተካሄደ ባለው የአካባቢ ጥበቃ ጉባዔ ላይ የተናገሩት፡፡

ግባችንን ለማሳካት በምናደርገው ጥረት ላይ ግን ማንም ፍጥነቱንም ሆነ ብልሃቱን እንዲነግረን አንፈልግም ነው ያሉት፡፡

 

Exit mobile version