Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የ65 አመት እድሜ ባለፀጋዋ ተመራቂ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 13 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) መምህርት የማርያምወርቅ ፀጋዬ ይባላሉ፤ ለረጅም አመታት በመምህርነት ሲያገለግሉ መቆየታቸውንም ይናገራሉ።

መምህርት የማርያምወርቅ ዛሬ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመጀመሪያ ዲግሪ ከተመረቁት መካከል አንደኛዋ ናቸው።

እኒህ እናት ለረጅም አመት ለመማር ፍላጎት ቢኖራቸውም ‘በተለያዩ ጫናዎች ምክንያት ሳይማሩ’ መቆየታቸውን ነው የሚናገሩት።

ታዲያ ይህ የመማር ፍላጎታቸው እውን ሆኖ በዛሬው ዕለት “ምኞቴን አሳክቻለሁ” ይላሉ።

ለዚህ ስኬት እንዲበቁ ደግሞ የልጆቻቸው፣ ቤተሰቦቻቸው እና የጓደኞቻቸው ድጋፍ ወደር የለውም ነው ያሉት።

አሁንም ሁለተኛ ዲግሪ ለመማር ፍላጎት እንዳላቸው የሚገልፁት መምህርት የማርያምወርቅ “ትምህርት በእድሜ የሚገደብ አይደለም” ብለዋል።

“ትምህርት ለስራ ማግኛ ወይም ለስራ ደረጃ እድገት የምንማረው መሆን የለበትም” የሚሉት መምህርት የማርያምወርቅ፥ “በተሻሻለ የኑሮ ዘይቤ ውስጥ ለመኖር ይጠቅማል” ሲሉም ያስረዳሉ።

 

በማርታ ጌታቸው

Exit mobile version