Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የሐረሪ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት የ2015 እቅድ አፈፃፀምን መገምገም ጀመረ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 13 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሐረሪ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት የ2015 በጀት ዓመት  እቅድ አፈፃፀምን መገምገም ጀምሯል፡፡

በመድረኩ በአመቱ በክልሉ የተከናወኑ አበይት ተግባራት በሚመለከት ሪፖርት ቀርቦ በካቢኔ አባላቱ እንደሚገመግም ተመላክቷል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም መስተዳድር ምክር ቤቱ በ2016 የበጀት አመት ረቂቅ በጀት ላይ እንደሚመክር ይጠበቃል።

 

እየተካሄደ በሚገኘው መድረክም የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪን ጨምሮ የካቢኔ አባላት  መገኘታቸውንከሐረሪ ክልል ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

Exit mobile version