Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

አቶ ደመቀ መኮንን ከቻይና ልዑካን ጋር መከሩ

 

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 14፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ የውጭ ግንኙነት ጉዳዮች ቢሮ ዳይሬክተር ዋንግ ዪ ከተመራው የልዑካን ቡድን ጋር ዛሬ በጽህፈት ቤታቸው ተወያይተዋል።

ከልዑካን ቡድኑ ጋር የተደረገው ውይይት በሁለትዮሽና እና የባለብዙ ወገን ጉዳዮች ላይ ያተኮረ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

ኢትዮጵያ እና ቻይና በዘርፈ ብዙ የሁለትዮሽ ቀጣናዊ እና ዓለም አቀፍ የጋራ ፍላጎቶች ላይ ተባብረው ለመስራት ዝግጁ መሆናቸው በውይይቱ ላይ ተገልጿል።

የቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ የውጭ ግንኙነት ጉዳዮች ቢሮ ዳይሬክተር ዋንግ ዪ ÷የቻይና ባለሀብቶች በኢትዮጵያ በኢንቨስትመንት ንግድና የዳግም ግንባታ መስኮች እንዲሰሩ መንግስታቸው እንደሚያበረታታ መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

Exit mobile version