አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 26፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የፐብሊክ ሰርቪስ ድርጅት ከረቡዕ ጀምሮ ተሳፋሪዎች የአፍ መሸፈኛ ጭንብል በአስገዳጅነት እንዲጠቀሙ ሊደርግ መሆኑን አስታወቀ።
የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ፍሬህይወት ትልቁ እንዳሉት አስገዳጅነቱ በሸገር እና ፐብሊክ ትራንስፖርት ተግባራዊ ይደረጋል።
ድርጅቱም ከተጠቀሰው ቀን ጀምሮ የአፍ መሸፈኛ ጭምብል የማይጠቀሙ ተሳፋሪዎችን እንደማይጭንም ነው የተናገሩት።
ዳይሬክተሯ ህብረተሰቡ የአፍ መሸፈኛ ጭምብል የመጠቀም ባህሉን ሊያሳድግ ይገባልም ነው ያሉት።
እንዲሁም የትራንስፖርት እጥረትን ለመፍታትም የመጫን አቅምን ከአስገዳጅ የአፍ መሸፈኛ አጠቃቀም ጋር በተያያዘ ወደ 43 የሚያድግ ይሆናል ብለዋል።
በሃይለየሱስ መኮንን
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

