አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሐዋሳ ቅዱስ ገብርኤል ክብረ በዓል በሰላም እንዲከበር የፀጥታ ዝግጅት ተጠናቆ ወደ ሥራ መገባቱን የክልሉ የፀጥታ ግብረ- ኃይል አስታወቀ፡፡
ግብረ- ኃይሉ ዓመታዊው የቅዱስ ገብርኤል ክብረ በዓል እና ወቅታዊ ክልላዊ የፀጥታ ሁኔታን አስመልክቶ በክልሉ ያለውን ነባራዊ ሁኔታ በመገምገም ትኩረት ሊሰጣቸው በሚገባቸው ጉዳዮች አቅጣጫ አስቀምጧል።
የሐዋሳ ቅዱስ ገብርኤል ክብረ በዓል ያለምንም የፀጥታ ችግር እንዲከበር በወጣው የፀጥታ ዕቅድ ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ተደርጎ ለፀጥታ ኃይሉ ስምሪት መሰጠቱ ተገልጿል፡፡
ከሐምሌ 18 ቀን 2015 ዓ.ም ከቀኑ 7:00 ጀምሮ ለተሽከርካሪ ዝግ የሚሆኑ መንገዶች መለየታቸውንም የክልሉ ፖሊስ መረጃ ያመላክታል፡፡
በዚህም አሽከርካሪዎች ዝግ የሚሆኑ መንገዶችን አውቀው አማራጭ መንገዶችን በመጠቀም ለፀጥታ አካላት አስፈላጊ ትብብር እንዲያደርጉ ተጠይቋል፡፡
ሕብረተሰቡ ከበዓሉ ጋር በተያያዘ ለሚያጋጥሙት ችግሮች 0462209164 የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን፣ 046 212 2468 የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን እና 0462201046 ሐዋሳ ፖሊስ መምሪያ በመደወል ጥቆማ እንዲሰጥም ጥሪ ቀርቧል፡፡