Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በድሬዳዋ የኩላሊት እጥበት ማዕከል ተመረቀ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ከ22 ነጥብ 7 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ በሳብያን ጠቅላላ ሆስፒታል ውስጥ የተገነባው የኩላሊት እጥበት ማዕከል ተመረቀ።

ማዕከሉ በውጭ ሀገራት በሚኖሩ የድሬዳዋ ተወላጆች ድጋፍና በናሽናል ሲሜንት አክሲዮን ማህበር ትብብር የተገነባ መሆኑ ተገልጿል።

በምርቃት ስነ-ስርዓቱ የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሃር፣ የድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ ኃላፊ ለምለም በዛብህ፣ በውጭ ሀገራት የሚኖሩ የድሬዳዋ ተወላጆች፣ የሀገር ሽማግሌዎችና የከተማው ነዋሪዎች ተገኝተዋል።

ማዕከሉ የማህበረሰቡን የኩላሊት እጥበት የሕክምና ችግር ለመፍታት ወሳኝ አበርክቶ እንዳለው መገለጹን የዘገበው ኢዜአ ነው።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version