Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በክልሉ ከ29 ሚሊየን ኩንታል በላይ ምርት ለመሰብሰብ እየተሠራ ነው – አቶ አሻድሊ ሀሰን

 

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በክልሉ በ2015/16 ምርት ዘመን 937 ሺህ 722 ሄክታር መሬት በዘር በመሸፈን ከ29 ሚሊየን ኩንታል በላይ ምርት ለመሰብሰብ እየተሠራ መሆኑን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ አሻድሊ ሀሰን ገለጹ።

ርዕሰ መስተዳድሩ የ2015 በጀት ዓመት የአስፈጻሚ አካላትን አፈጻጸም ለክልሉ ምክር ቤት ባቀረቡበት ወቅት እንደገለጹት፤ የግብርናውን ዘርፍ በትኩረት በመምራት የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ ባለፈ ዋነኛ የኢኮኖሚው ዕድገት ምንጭ ለማድረግ እየተሠራ ነው።

በተያዘው የመኸር ወቅት ደግሞ 937 ሺህ 722 ሄክታር መሬት በዘር በመሸፈን ከ29 ሚሊየን 129 ሺህ 851 ኩንታል ምርት ለመሰብሰብ እየተሠራ መሆኑን አቶ አሻድሊ አስታውቀዋል።

እስካሁንም 675 ሺህ 723 መሬት የታረሰ ሲሆን÷ 576 ሺህ 270 መሬት ደግሞ በዘር መሸፈኑን ነው የገለጹት።

በተጨማሪም በክረምቱ 50 ሺህ ሄክታር መሬት በስንዴ ዘር እንደሚሸፈን ጠቁመው ከዚህም 2 ሚሊየን ኩንታል ምርት እንደሚጠበቅ ጠቅሰዋል።

በክልሉ መንግስት የተገዙ እና በተለያዩ ድጋፎች የተገኙ 98 ትራክተሮችን ለተጠቃሚዎች የማድረስ ሥራ እየተከናወነ መሆኑን መናገራቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

Exit mobile version