Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በከፍተኛ ሙቀት ምክንያት በተከሰተ ሰደድ እሳት ከ40 በላይ ሰዎች ለህልፈት ተዳረጉ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በከፍተኛ ሙቀት ምክንያት በተከሰተ ሰደድ እሳት ከ40 በላይ ሰዎች ለህልፈት መዳረጋቸው ተሰማ።

በአልጄሪያ፣ ጣሊያን እና ግሪክ የሰደድ እሳቱ ወደመንደሮችና መዝናኛ ቦታዎች ላይ በመስፋፋቱ የዜጎች ህይወት ማለፉ የተገለጸው፡፡

ከዚህ ባለፈም በሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች ከመኖሪያ ቀያቸው ለቀው እንዲወጡ መደረጉን ቢቢሲ አስነብቧል፡፡

ሰደድ እሳቱ በሜዲትራንያን ባህር አካባቢ ባሉ ሀገራት ዙሪያ በተከሰተው የሙቀት ማዕበል ሳቢያ የተቀሰቀሰ መሆኑን የሚቲዮሮሎጅ ትንበያ ባለሙያዎች አመላክተዋል።

በግሪክ ኮርፉ እና ኢቪያ በተባሉ ደሴቶች ላይ የሚኖሩ የኅብረተሰብ ክፍሎች አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ ትዕዛዝ መተላለፉ የሚታወቅ ሲሆን፥ በደሴቶቹ ላይ የእሳት ቃጠሎ ስለሚነሳ ግሪክ ከሮድስ ተጨማሪ በረራዎች ለማድረግ በዝግጅት ላይ ትገኛለችም ነው የተባለው።

በአንዳንድ የሀገሪቱ አካባቢዎች የሙቀት ማዕበሉ ከ44 ዲግሪ ሴሊሺየስ በላይ ሊደርስ እንደሚችልም ተነግሯል፡፡

በተጨማሪም በሲሲሊ እና ፑግሊያ በተነሳው የእሳት ቃጠሎ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች እንዲሰደዱ አድርጓል።

ከፍተኛ ንፋስ እና የደረቁ እፅዋት የእሳት አደጋ መከላከል ሰራተኞች ሰደድ እሳቱን ለመቆጣጠር በሚያደርጉት ጥረት ፈተና እንደሆነባቸውም ነው የተገለጸው፡፡

እስካሁን ከፍተኛው የሟቾች ቁጥር በአልጄሪያ የተመዘገበ ሲሆን፥ ነዋሪዎችን ከእሳት አደጋ ለማስወጣት ጥረት ላይ የነበሩ 10 ወታደሮችን ጨምሮ 34 ሰዎች ለህልፈት ተዳርገዋል ነው የተባለው።

ሰደድ እሳቱ በሰው ህይወት ላይ እስካሁን ጉዳት ባያደርስም በሊቢያ መከሰቱንን በአነስተኛ መንደር ላይ ከፍተኛ ውድመት ማድረሱን ዘገባው የሚያመላክተው።

የአየር ንብረት ተመራማሪዎች በዚህ ወር በደቡብ አውሮፓ ፣ በሰሜን አሜሪካ እና በቻይና ያለው ከፍተኛ የሙቀት ማዕበል በሰው ሰራሽ የአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት የተከሰተ እንደሆነ ገልጸዋል።

በተመሳሳይ በጣሊያን ሰሜናዊ ክፍል ከፍተኛ አውሎ ንፋስ ፣ በሲሲሊና ሌሎች የሀገሪቱ ክፍሎች ደግሞ ከፍተኛ ሰደድ እሳት መከሰቱም ታውቋል፡፡

በዚህም በእድሜ የገፉ ጥንዶችን ጨምሮ ሌሎችም ለህልፈት ተዳርገዋል ነው የተባሉት፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version