Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በትግራይ ክልል ከ55 ሺህ በላይ ታጣቂዎች ወደ ሕብረተሰቡ ተቀላቀሉ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በትግራይ ክልል የነበሩ ከ55 ሺህ በላይ ታጣቂዎች ወደ ሕብረተሰቡ መቀላቀላቸውን የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ም/ርዕሰ መስተዳድርና ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ ጀነራል ታደሰ ወረደ ገለጹ፡፡

ጀነራል ታደሰ ወረደ ዛሬ በሰጡት መግለጫ÷ በፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት መሰረት ከ55 ሺህ በላይ ታጣቂዎች ወደ ሕብረተሰቡ እንዲቀላቀሉ በክብር ሽኝት ተደርጎላቸዋል ብለዋል፡፡

ይህም የትግራይ ሕዝብ ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን ያለውን ዝግጁነት ያሳያል ነው ያሉት፡፡

ወደ ሕብረተሰቡ የተቀላቀሉ የቀድሞ ታጣቂዎችን ለማቋቋም ቀጣይነት ያላቸው የተለያዩ ፕሮጀክቶች እንደሚሠሩ አንስተዋል፡፡

ሽኝት የተደረገላቸው የቀድሞ ታጣቂዎችም በክልሉ በተለያዩ ወረዳዎች አቀባበል እየተደረገላቸው ነው ማለታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ ያመላክታል፡፡

Exit mobile version