አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የጣሊያን የሥነ-ምኅዳር ዘላቂነት ሚኒስቴር በኮቪድ -19 ወረርሽኝ ምክንያት በኢትዮጵያ አቋርጧቸው የነበሩ ፕሮጀክቶችን ዳግም ሥራ እንዲጀምሩ ለማድረግ ከስምምነት ደርሷል፡፡
በዓለም የሥርዓተ- ምግብ ጉባዔ እየተሳተፉ ያሉት የኢትዮጵያ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ጌታሁን ጋረደው (ዶ/ር) ከመደኛ ስብሰባቸው ጎን ለጎን ከጣሊያን የሥነ-ምኅዳር ዘላቂነት አመራሮች ጋር መክረዋል፡፡
በውይይታቸውም÷ ጣሊያን በኢትዮጵያ የአካባቢ ዘላቂነት እንዲረጋገጥ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንድትቀጥል ዋና ዳይሬክተሩ ጠይቀዋል፡፡
የጣሊያን የሥነ-ምኅዳር ዘላቂነት ሚኒስቴር አመራሮችም÷ በኮቪድ- 19 ወረርሽኝ ምክንያት ተቋርጠው የነበሩ ፕሮጀክቶች በአጭር ጊዜ ሥራ እንዲጀምሩ ከስምምነት መድረሳቸውን የባለስልጣኑ መረጃ ያመላክታል፡፡