Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት አስተባባሪነት በአሶሳ የክረምት በጎ ፈቃድ ስራዎች እየተከናወኑ ነው

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስተባባሪነት የፌዴራል እና የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ቡድን የክረምት በጎ ፈቃድ ስራዎችን በአሶሳ እያካሄዱ ነው።

ዓላማው ሃገራዊ አንድነትን ማጠናከር መሆኑን በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር ዴኤታ እና የዝግጅቱ አስተባባሪ አቶ ተስፋዬ ዳባ ገልጸዋል።

የክልሉ ርዕሰ-መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሃሰን በበኩላቸው÷ ሀገራዊ ፕሮግራሙ የክልሉን እና ሀገራዊ የክረምት በጎ ፈቃድ ስራ አቅድን ለማሳካት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው ተናግረዋል።

መርሐ-ግብሩ በህብረተሰቡ መካከል መተሳሰብ እና አብሮነትን እንደሚያጎለብት ነው ያስረዱት፡፡

ቡድኑ በክረምት በጎ ፈቃድ ስራው የሁለተኛው ምዕራፍ የአረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብር አካል የሆነውን የችግኝ ተከላ መርሐ-ግብሩ በአሶሳ ከተማ ኢንዚ ተራራ ላይ ማከናወኑን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በተጨማሪም በአሶሳ ከተማ እና አካባቢው የሚገኙ የአቅመ ደካማ ወገኖች መኖሪያ ቤቶች ጥገና እና እድሳት ስራ በተጨማሪም የት/ቤት ግንባታ ያስጀምራል ተብሎ ይጠበቃል።

 

 

Exit mobile version