አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ገቢዎች ቢሮ በ2015 በጀት ዓመት ከ5 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን አስታወቀ።
ቢሮው ከመደበኛና ከማዘጋጃ ቤት ገቢ ከ 4ነጥብ 1 ቢሊየን ብር በላይ ለመሰብሰብ አቅዶ ከእቅዱ በላይ መሰብሰቡን የቢሮው ሃላፊ ወይዘሮ ህይወት አሰግድ ገልጸዋል።
በክልሉ ለመጀመሪያ ጊዜ የደረጃ “ሐ “ግብር ከፋዮች የዕለት ገቢ ግመታ በተሳካ መልኩ መከናወኑን የገለጹት ሀላፊዋ ክልሉ ከሚያመነጨው ኢኮኖሚ ገቢን በፍትሃዊነት ለመሰብሰብ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡
በ2016 በጀት አመት ከመደበኛና ማዘጋጃ ቤታዊ ገቢ ከ6 ነጥብ2 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ለመሰብሰብ መታቀዱንም ተናግረዋል።
በተስፋዬ ምሬሳ