Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የግብርና ኢኮኖሚያችንን ማሳደግ የሚያስችሉ አዳዲስ ኢኒሼቲቮችን ቀርፀን ወደ ስራ ገብተናል-ርእሰ መስተዳድር ሽመልስ

 

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የግብርና ኢኮኖሚያችንን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የሚያስችሉ የተለያዩ አዳዲስ ኢኒሼቲቮችን ቀርፀን ወደ ስራ ገብተናል ሲሉ የኦሮሚያ ክልል ርእሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ ተናገሩ፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው÷”ግብርናችን በምርምርና ቴክኖሎጂ ከተደገፈ በግብርናው ዘርፍ ለማሳካት የያዝናቸው ትላልቅ ስትራቴጂካዊ እቅዶች በማሳካት የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ፣ የስራ እድሎችን በስፋት መፍጠር፣ ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን ማስቀረት እና የውጭ ምንዛሪን በማስገኘት የምናሳካ ይሆናል” ብለዋል።

ከዚህ በመነሳት የኦሮሚያ ክልል ኢኮኖሚያችንን ሊያሸጋግሩ የሚችሉ ከ300 በላይ ኢንሼቲቮችን አጥንቶ ተግባራዊ ያደረገ መሆኑን ጠቅሰው በአሁኑ ወቅት 28 የግብርና ኢኒሼቲቮች ተግባራዊ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡

በቅርቡ ከተተገበሩት የግብርና ኢኒሼቲቮች መካከልም የኢሉ ገላን የሙዝ ልማት ኢኒሼቲቭ ዲክላሬሽን አንዱ መሆኑንም ተናግረዋል።

ቀደም ሲል ወደ ሀገር ውስጥ ሲገባ የነበረው የሙዝ ዘርን በማባዛትና የማከፋፈል ስራው ተጨባጭ ውጤት እያስመዘገበ ሲሆን÷ በአሁኑ ወቅትም በምዕራብ ሸዋ ዞን ኢሉ ገላን ወረዳ ብቻ ከ100 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በሙዝ ማልማት ተችሏል ነው ያሉት።

Exit mobile version