Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በደቡብ ክልል ከ573 ኩንታል በላይ የአፈር ማዳበሪያ በሕገ- ወጥ መንገድ ሲዘዋወር ተያዘ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 21፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች በሕገ- ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ 573 ነጥብ 5 ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ መያዙ ተገለጸ።

በፍርድ ቤት ውሳኔ የተሰጠበት የአፈር ማዳበሪያ በፍጥነት ለአርሶ አደሩ እንዲሰራጭ እየተደረገ መሆኑም ተጠቁሟል።

የደቡብ ክልል ኅብረት ሥራ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አምሪያ ሲራጅ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት÷ በክልሉ ያለውን የአፈር ማዳበሪያ እጥረት ተከትሎ በተለያየ አካባቢ ሕገ-ወጥ እንቅስቃሴ ተስተውሏል፡፡

ለአብነትም በጉራጌ፣ ጎፋ እና ጌዴኦ ዞኖች ውስጥ በሚገኙ አምስት ወረዳዎች 573 ነጥብ 5 ኩንታል ማዳበሪያ ሲያዘዋውሩ የተገኙ ስድስት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተካሄደ ነው ብለዋል፡፡

ከተያዘው የአፈር ማዳበሪያ መካከል በፍርድ ቤት ጥቅም ላይ እንዲውሉ ውሳኔ የተሰጠበትን ማዳበሪያ ለአርሶ አደሩ ማሰራጨታቸውን እና ቀሪው በሂደት ላይ ስለመሆኑ ተናግረዋል፡፡

በዮሐንስ ደርበው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version