Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ባለፉት 7 ወራት 102 የዓይን ብሌን ንቅለ ተከላ ተከናወነ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 21፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ከፈረንጆቹ ጥር ወር 2023 ጀምሮ 102 የዓይን ብሌን ንቅለ ተከላ ማከናወኑን የኢትዮጵያ ዓይን ባንክ አስታወቀ፡፡

የባንኩ ሜዲካል ዳይሬክተር እና በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የዓይን ትምህርት ክፍል መምህርት ዶ/ር መነን አያሌው÷ ባለፈው የፈረንጆቹ ዓመት ከሕልፈት በኋላ 191 የዓይን ብሌን ለመለገስ ቃል መገባቱን አስታውሰዋል፡፡

የተያዘው የፈረንጆቹ ዓመት ከገባ ጀምሮም ከሕልፈት በኋላ 323 የዓይን ብሌን ለመለገስ ቃል መገባቱን ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል፡፡

ይህም የዓይ ብሌን ከመለገስ ጋር በተያያዘ በሕብረተሰቡ ዘንድ ያለው አመለካከት እየተሻሻለ መሆኑን ቢያሳይም÷ ከሚፈለገው የዓይን ብሌን አንጻር ግን በቂ እንዳልሆነ አስገንዝበዋል፡፡

የዓይን ብሌን የመለገስ ባሕሉ ዝቅተኛ መሆንበዕቅድ መሰረት ለመሥራት እንዳላስቻለም ገልጸዋል፡፡

ለአብነትም በ2022፥ 243 የዓይን ብሌን ንቅለ ተከላ ለማከናወን ታቅዶ 223 መከናወኑን አስታውሰዋል፡፡

“ብሌናችንን እንለግስ፤ ብርሃን አንቅበር” ሲሉም ሕብረተሰቡ ከሕልፈት በኋላ የዓይን ብሌኑን እንዲለግስ ጥሪ አቅርበል።

በዮሐንስ ደርበው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version