Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በኦሮሚያ ክልል በ5 ቢሊየን ብር ወጪ 1 ሺህ 395 ኪ.ሜ የመንገድ ግንባታ ስራ ተከናወነ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 21፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል በ2015 በጀት ዓመት 5 ቢሊየን ብር በሚጠጋ ወጪ 1 ሺህ 395 ኪሎ ሜትር አዲስ የመንገድ ግንባታ ስራ መከናወኑን የክልሉ መንገዶችና ሎጂስቲክስ ቢሮ አስታውቋል፡፡

በቢሮው የእቅድ ዝግጅት እና ክትትል ግምገማ ዳይሬክተር አሸናፊ ሃብታሙ እንደገለጹት÷ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በክልሉ የትራንስፖርት ፍሰትን የሚያሳልጡ በርካታ መንገዶች ተገንብተዋል፡፡

በዚህ መሰረት በበጀት ዓመቱ 5 ቢሊየን ብር በሚጠጋ ወጪ 1 ሺህ 395 ኪሎ ሜትር አዲስ የመንገድ ግንባታ ስራ መከናወኑን አንስተዋል፡፡

የመንገድ ግንባታዎቹ በክልል እና በዞን ደረጃ ክትትል የሚደረግባቸው መሆኑንም ነው ዳይሬክተሩ የጠቆሙት፡፡

ከተገነቡት መንገዶች ውስጥ 119 ኪሎ ሜትር የሚሆነው በካፒታል ፕሮጀክት ደረጃውን በጠበቀ መልኩ መገንባቱን ተናግረዋል፡፡

የገጠር መንገድ ተደራሽነትን ለማስፋት በተከናወነ ስራም 1 ሺህ 395 ኪሎ ሜትር የገጠር መንገድ ግንባታ መከናወኑን ገልጸዋል፡፡

በቀጣይ ዓመትም የትራንስፖርት ፍሰቱን የሚያሳልጡ አዳዲስ መንገዶችን መገንባት የሚያስችል 5 ነጥብ 1 ቢሊየን ብር በጀት መያዙን ጠቅሰዋል፡፡

በመላኩ ገድፍ

Exit mobile version