አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 21፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሌ ክልል የብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች የግምገማ መድረክ በጅግጅጋ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡
የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሐመድን ጨምሮ የካቢኔ አባላት፣ ምክትል ቢሮ ኃላፊዎች እና በክልል ደረጃ ያሉ ተቋማት አመራሮች በመድረኩ ተገኝተዋል፡፡
በብልጽግና ፓርቲ የሶማሌ ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ መሐመድ ሻሌ (ኢ/ር) እንዳሉት÷ በመድረኩ አመራሩ በ2015 ዓ.ም የፓርቲው ስራዎች ላይ ያሳየው አፈፃፀም እና ያሳካቸው ውጤቶች ላይ ትኩረት ይደረጋል፡፡
በፓርቲው አቅጣጫ መሠረትም÷ አመራሩ ኃላፊነቱን እና ፓርቲው የጣለበትን ግዴታ ስለመወጣቱ እንዲሁም ዜጎችን በአግባቡ ስለማገልገሉ የሚሉትን ጨምሮ ሌሎች ነጥቦች የግምገማው ትኩረት ናቸው ብለዋል፡፡
የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ በበኩላቸው ግምገማው አመራሩ የተመደበበትን ሥራ በአግባቡ መወጣቱ የሚፈተሽበት ነው ማለታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ ያመላክታል፡፡
በክልሉ ጠንካራና ብቃት ያላቸው አመራሮችን ለማፍራት እና የተጀመሩትን ሥራዎች ለማገዝ የመድረኩ ሚና ከፍተኛ መሆኑንም አመላክተዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!