Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የጋራ አረዳድ በመፍጠር የተጀመረው የሠላም ሂደት እንዲጠናከር መስራት ይገባል – ይልቃል ከፋለ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 25፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በወቅታዊ የሰላምና የጸጥታ ሁኔታዎች ላይ የጋራ አረዳድ በመፍጠር የተጀመረው የሠላምና የልማት ሂደት እንዲጠናከር መስራት እንደሚገባ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

ይልቃል ከፋለ (ዶ/ር)÷ከአማራ ክልል ከሁሉም ዞኖች ከተወጣጡ የሃይማኖት አባቶች እና የሀገር ሽማግሌዎች ጋር በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ በባህር ዳር ከተማ እየመከሩ ነው።

ክልላዊ ወቅታዊ ፖለቲካዊ አዝማሚያዎችን እና የሠላምና የፀጥታ ሁኔታዎችን አመላካች መነሻ ሃሳብ ርዕሰ መስተዳድሩ አቅርበዋል፡፡

የውይይት መድረኩ በወቅታዊ የሰላምና የጸጥታ ሁኔታዎችና አዝማሚያዎች ላይ የጋራ አረዳድ በመፍጠር የተጀመረው የሠላምና የልማት ሂደቱ እንዲጠናከር ፋይዳው የጎላ መሆኑ ተገልጿል።

የአማራ ክልል ሕዝብ ጦርነት ሳይሆን ልማት የሚሻ ህዝብ በመሆኑ ልማት ላይ በማተኮር የህዝቡት ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ይገባል መባሉንም የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

Exit mobile version