አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 26፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ክልል የ2016 በጀት 55 ቢሊየን 836 ሚሊየን 723 ሺህ 309 ብር ሆኖ እንዲጸድቅ ለክልሉ ምክር ቤት የውሳኔ ሐሳብ ቀረበ፡፡
የደቡብ ክልል መስተዳድር ምክርቤት ዛሬ ባካሔደው 254ኛ መደበኛ ስብሰባው በ2016 ረቂቅ በጀት ላይ ተወያይቷል፡፡
በውይይቱም÷ በክልሉ ለ2016 የቀረበው ረቂቅ በጀት ከፌደራል መንግስት ድጎማ 28 ቢሊየን 748 ሚሊየን 375 ሺህ 845 እንዲሁም ከክልሉ ገቢ 26 ቢሊየን 740 ሚሊየን 994 ሺህ 239 የሚገኝ መሆኑ ተገልጿል፡፡
የ2016 በጀት የ20 ነጥብ 6 በመቶ ዕድገት አለው መባሉን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡
ምክር ቤቱ በቀረበው የክልሉ መንግስት የ2016 በጀት ረቂቅ አዋጅ ላይ ተወያይቶ ግብአቶችን በማከል ወደ ክልሉ ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ ወስኗል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!