Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በኦሮሚያ ክልል 225 ሺህ 395 ሄክታር በለውዝ ሰብል ተሸፍኗል

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ከተዘጋጀው 225 ሺህ 679 ሄክታር 225 ሺህ 395 ሄክታር መሬት በለውዝ ሰብል መሸፈኑን የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ ገለጹ፡፡

አቶ ሽመልስ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በኢኒሼቲቭ ልማት ትኩረት አድርጎ ከሚሰራባቸው ስራዎች አንዱ የለውዝ ልማት ነው ብለዋል፡፡

የኢኒሼቲቭ ልማት ስራዎችን በማጠናከር ጠንካራ የሆነ ኢኮኖሚ እንገነባለንም ሲሉም ገልጸዋል፡፡

በዚህ ዓመት 200 ሺህ ሄክታር በለውዝ ለማልማት ታቅዶ እንደነበር አስረድተዋል፡፡

የኢትዮጵያ መሬት የተሰጠውን ማብቀል ብቻ ሳይሆን እንደ ለውዝ ያሉ ወደ ውጭ በመላክ ላይ ትልቅ ጠቀሜታ ያላቸውን ምርቶችን ለማምረት ምቹ ስለመሆኑ አስገንዝበዋል፡፡

አሁንም ለህብረተሰቡ ኢኮኖሚ ጠቃሚ የሆኑ ምርቶች ላይ በማተኮር የውጪ ኤክስፖርትን ለማሳደግ በቁርጠኝነት እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version