Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የት/ት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀትን በቴክኖሎጂ ማረጋገጥ የሚያስችል ስምምነት ተፈረመ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የትምህርት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀትን በቴክኖሎጂ ማረጋገጥ የሚያስችል ስምምነት ተፈረመ።

የመግባቢያ ሰነዱ ደህንነቱ የተጠበቀ የትምህርት ማስረጃ የምስክር ወረቀት ለተመደቡ ተቋማት መስጠት ያስችላል ተብሏል፡፡

ስምምነቱን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር፣ የኢፌዴሪ የትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን እና “ኤስ አይ ሲ ፒ ኤ” ተፈራርመዋል።

የስምምነቱ ዓላማ ከጊዜ ወደጊዜ እየተስፋፋ የመጣውን ሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃ ለመቆጣጠርና ደህንነቱ የተጠበቀ የትምህርት ማስረጃ እውነተኛነትን ለማረጋገጥ መሆኑን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

በስምምነቱ መሰረት ለተመረጡ ስድስት የትምህርት ተቋማት 4 ሺህ የደህንነት ማረጋገጫ ኮድ በመስጠት ሙከራው እንደሚጀመር ተገልጿል፡፡

በተጨማሪም የስምምነቱ ትግበራ ከተፈረመበት ቀን ጀምሮ በስድስት ወራት ውስጥ የሚጀመር ይሆናል ነው የተባለው።

Exit mobile version