አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ሕንድ የኢትዮጵያን የንግድ እና የኢንቨስትመንት አማራጮች ለማስተዋወቅና ከኢትዮጵያ ኤምባሲ ጋር በትብብር ለመስራት ያላትን ዝግጁነት ገለጸች፡፡
በሕንድ የኢትዮጵያ አምባሳደር ደመቀ አጥናፉ ከንግድ፣ ዘላቂ ልማት እና የውጭ ግንኙነት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት እና ዋና ስራ አስፈፃሚ አቢናቭ ባያን ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸውም ፥ በኢትዮጵያ የንግድ እና የኢንቨስትመንት አማራጮች ላይ ትኩረት አድርገዋል፡፡
አምባሳደር ደመቀ በኢትዮጵያ ስላለው የንግድና የኢንቨስትመንት አማራጮች ላይ ባደረጉት ገለፃ የሁለቱን ሀገራት የቆየ ግንኙነት በጋራ ተጠቃሚነት ላይ የተመሰረተ ለማድረግ የኢትዮጵያ መንግስት ቁርጠኛ መሆኑን መግለጻቸውን ከኤምባሲው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ፖሊሲና የንግድ ሁኔታ ላይ አመርቂ ማሻሻያዎችን በማድረግ ሀገሪቱን ለውጭ ባለሃብቶች ተመራጭ እንድትሆን መንግስት ከፍተኛ ጥረት አድርጓልም ብለዋል አምባሳደሩ።
ፕሬዚዳንቱ እና ዋና ስራ አስፈፃሚ አቢናቭ ባያን በበኩላቸው፥ የንግድ ምክር ቤቱ በሕንድ ተከታታይ ሴሚናሮችን በማካሄድ ከኤምባሲው ጋር በትብብር ለመስራትና የኢትዮጵያን የንግድ እና የኢንቨስትመንት አማራጮች ለማስተዋወቅ ያለውን ዝግጁነት ገልጸዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!