Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የጤና ሚኒስቴር በሁሉም ክልሎች ድጋፋዊ ክትትልና ጉብኝት ሊያደርግ ነው

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 29፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የጤና ሚኒስቴር በሁሉም ክልሎች ድጋፋዊ ክትትልና ጉብኝት ሊያደርግ መሆኑን አስታወቀ።

በሁሉም ክልሎች የሚካሄደው ድጋፋዊ ክትትልና ጉብኝት ግንቦት 3 2012 ዓ.ም ጀምሮ የሚካሄድ መሆኑን ሚኒስቴሩ ባወጣው መረጃ አመላክቷል።

ድጋፋዊ ክትትሉ በዋናነት የሚደረገው ከኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ 19) ውጭ ባሉ መደበኛ ስራዎች ላይ መሆኑንም ሚኒስቴሩ አስታውቋል።

አሁን ባለው ሁኔታ ከሆስፒታል እስከ ጤና ኬላዎች በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ 19) ወረርሽኝ ምክንያት በመደበኛ የሕክምና ስራዎች ላይ ከፍተኛ መቀዛቀዝ ተስተውለዋል።

በመሆኑም ወጥ የአሰራር መመሪያ እና መከታተያ በሁሉም ክልሎች ያሉ ጤና ተቋማት አሰራር በምን ሁኔታ ላይ እንደሆኑና የቢሮ አደረጃጀታቸው ምን እንደሚመስል በመጎብኘት ድጋፍም እንደሚደረግላቸው ሚኒስቴሩ አስታውቋል።

የጤና ሚኒስትር ደኤታው ዶክተር ደረጄ ዱጉማ፥ ድጋፋዊ ጉብኝቱ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ተቀዛቅዞ የነበረውን የመደበኛ ሕክምና አገልግሎት ወደ ነበረበት ለመመለስ ከተቻለም ከዚያም ለማሻሻልል መከናወን እንደሚኖርበት ገልፀዋል።

Exit mobile version