Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ኢትዮጵያና ብሪታንያ ወዳጅነታቸውን በሚያጠናክሩ ጉዳዮች ላይ ምክክር ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ እና ብሪታንያ የፓርላማ የወዳጅነት ቡድን አባላት የሁለቱ ሀገራት ታሪካዊ ግንኙነት የበለጠ ተጠናክሮ በሚቀጥልበት ሁኔታ ላይ ተወያይተዋል።

በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነት እና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ዲማ ነጎ (ዶ/ር)÷ ኢትዮጵያ እና ዩናይትድ ኪንግደም የረጅም ጊዜ መልካም ግንኙነት እንዳለቸው ገልጸዋል፡፡

ግንኙነቱን የበለጠ ለማጠናከር በንግድና ኢኮኖሚ፣ በኢንቨስትመንት እና መሰል ዘርፎች በትብብር መሰራት እንደሚያስፈልግም ነው ያመላከቱት፡፡

ሁለቱ ሀገራት በዓለም አቀፍ መድረኮች ላይ ተሰሚነታቸውን መጨመር በሚያስችሉ ሁኔታዎችም በትብብር እንደሚሰሩ መምከራቸውን የምክር ቤቱ መረጃ ያመላክታል፡፡

የብሪታንያ የፓርላማ አባል አሊሻ ኬርንስ በበኩላቸው÷ የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር በንግድ፣ በኢንቨስትመንት፣ በትምህርት እና በተለያዩ ዘርፎች በትብብር እንደሚሰሩ ተናግረዋል ።

የፓርላማ ተግባራትን ለማጠናከር የልምድ ልውውጥ ማድረግ እንደሚገባም አንስተዋል የሁለቱም ሀገራት የፓርላማ የወዳጅነት ቡድን አባላት።

Exit mobile version