Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

አይካ አዲስ ጨርቃጨርቅ ፋብሪካን ወደ ስራ ለማስገባት እየተሰራ ነው

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ቀድሞ አይካ አዲስ ተብሎ ይጠራ የነበረውና በአዲስ መልክ ተደራጅቶ ቡሉኮ ኢንቲግሬትድ ጨርቃጨርቅ የሚል ስያሜ ያገኘውን ፋብሪካፋ ወደ ስራ ለማስገባት እየተሰራ መሆኑን የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ገለጸ።

የሚኒስቴሩ ከፍተኛ አመራሮች በፋብሪካው ጉብኝት አድርገው ከሚመለከታቸዉ አካላት ጋር ተወያይተዋል።

አይካ አዲስ ጨርቃጨርቅ ፋብሪካ ላለፉት 4 ዓመታት ስራ አቁሞ የነበር ሲሆን በስሩ ከ7 ሺህ በላይ የስራ ዕድል የፈጠረ እና ትልቅ ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ የነበረው ፋብሪካ እንደነበረ ተገልጿል።

የከፍተኛ አመራሩ የመስክ ጉብኝት ዋና አላማም ፋብሪካው ከሚፈጥረው በርካታ የስራ ዕድል በተጨማሪ ለሀገር የሚያበረክተው ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ከፍተኛ በመሆኑ ዳግም ወደ ስራ ለማስገባት ያለመ ነው፡፡

በተጨማሪም ፋብሪካውን በአዲስ መልክ ወደ ስራ ለማስገባት እየተደረገ ያለውን ጥረት ለመደገፍና አስፈላጊውን እገዛ ማድረግም የጉብኝቱ አላማ እንደሆነ ተጠቅሷል።

ፋብሪካውን የኦሮሚያ የልማት ድርጅት ከግል ከባለሀብቶች ጋር በመሆን ወደ ስራ ለማስባት እየሰሩ መሆኑን ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ አመልክቷል።

በሚኒስቴሩ የተጀመረው የኢትዮጵያ ታምርት ሀገራዊ ንቅናቄ የተዘጉና ስራ ያቆሙ ኢንዱስትሪዎች ወደ ስራ እንዲገቡ የሚያደርገውን የድጋፍና ክትትል ማዕቀፍ መሰረት በማድረግ አስፈላጊው ድጋፍ ለፋብሪካው እንደሚደረግም ተጠቁሟል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version