Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ከ247 ሚሊየን ብር በላይ ዋጋ ያለው ኮኬይን ተያዘ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት 29 ነጥብ 2 ኪሎ ግራም የሚመዝን ኮኬይን ተያዘ፡፡

የተያዘው ኮኬይን የተባለ አደንዛዥ እጽ 247 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር ግምታዊ ዋጋ አለው መባሉን የጉምሩክ ኮሚሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

አደንዛዥ እጹ መነሻውን ብራዚል ባደረገ አውሮፕላን ተጭኖ ነው ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የደረሰው፡፡

የአዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ሰራተኞች ባደረጉት ፍተሻ ሊያዝ ችሏል፡፡

በተጨማሪም የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን መምሪያ፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሰራተኞች፣ የፌደራል ፖሊስ አመራሮች አደንዛዥ እጹ እንዲያዝ ከፍተኛ ጥረት ማድረጋቸው ተመላክቷል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version