Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

አቶ ሙስጠፌ ወርቃማውን የወጣትነት አቅም ለልማት መጠቀም ይገባል አሉ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 6፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ሙስጠፌ መሐመድ ወርቃማውን የወጣትነት ዕድሜ እና አቅም በተገቢው መንገድ ለልማት መጠቀም እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡

በዓለም ለ23ኛ በኢትዮጵያ ለ20ኛ ጊዜ የተከበረው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ዛሬ በሶማሌ ክልል አቶ ሙስጠፌ መሐመድ እና የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) በተገኙበት ተከብሯል፡፡

ቀኑ የተከበረው የበጎ ፈቃድ አገልግሎቶችን ጨምሮ የተለያዩ መርሐ ግብሮችን በማከናወን መሆኑን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ ያመላክታል፡፡

ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር)በአከባበሩ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ ወጣቶች ልዩነትን በሰለጠነ መንገድ በውይይት የመፍታት ልምድን በማዳበር የራሳቸውን መልካም አስተዋጽኦ ማበርከት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version