Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

አቶ ጌታቸው ረዳ የትግራይ ወጣቶች ለሰላምና ልማት ግንባታ የድርሻቸውን እንዲወጡ ጠየቁ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 6፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የክልሉ ወጣቶች የተገኘውን ሰላም ዘላቂ ለማድረግና የልማት ግንባታን ለማፋጠን የድርሻቸውን ሊወጡ እንደሚገባ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር ጌታቸው ረዳ ገለጹ።
ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ዛሬ በመቀሌ ከተማ በፓናል ውይይት ተከብሯል፡፡
አቶ ጌታቸው ረዳ በአከባበሩ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ የተገኘውን ሰላም ጠብቆ ልማትና እድገት እንዲረጋገጥ ወጣቶች ግንባር ቀደም ሚና ሊጫወቱ ይገባል ብለዋል።
ወጣቶች ያላቸውን እውቀትና ጉልበት አሟጠው በመጠቀም ለማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እድገት መፋጠን የድርሻቸውን መወጣት እንዳለባቸውም አሳስበዋል።
የአካበበሩ ተሳታፊ ወጣቶች በበኩላቸው÷ ሰላምና ልማት ለማረጋገጥ እየተደረገ ባለው እንቅስቃሴ በመሳተፍ የድርሻቸውን እንደሚወጡ አረጋግጠዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version