አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 8፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ለ2016 የትምህርት ዘመን የመማሪያና ማስተማሪያ መጽሐፍትን በወቅቱ ለተማሪዎች ለማድረስ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት እየሠራ መሆኑን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ትምህርት ቢሮ ገለጸ።
ለትምህርት ዘመኑ 1 ሚሊየን 506 ሺህ 957 የመማሪያና ማስተማሪያ መጽሐፍት እንደሚያስፈልግ የቢሮው ምክትል ኃላፊ ደረሰ ጋቲሳ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ገልፀዋል።
ለኅትመቱ 369 ሚሊየን ያህል ብር እንደሚያስፈልግ ጠቁመው÷ ወጪውም በክልሉ መንግሥት፣ በሕብረተሰቡ ተሳትፎና በዞን አስተዳደሮች ይሸፈናል ብለዋል።
ከ1ኛ እስከ 12ኛ ክፍል 845 ሺህ 427 ተማሪዎች በትምህርት ገበታ ላይ እንደሚገኙ ታቅዶ፥ ተማሪዎች በትምህርት ዓይነት በዴስክ አንድ መጽሐፍ እንዲያገኙ ለማድረግ እየተሠራ መሆኑን ተናግረዋል።
ከ7ኛ እስከ 8ኛ ከፍል ላሉ ተማሪዎች እስካሁን 175 ሺህ 834 መጽሐፍት ወደ ትምህርት ቤቶች መሰራጨታቸውንም አረጋግጠዋል።
ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ላሉ ተማሪዎች የሚሆን መጽሐፍ በትምህርት ሚኒስቴር በኩል እየታተመ ስለመሆኑም አመላክተዋል።
ከ1ኛ እስከ 6ኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎች በአፍ መፍቻ ቋንቋ እንደሚማሩ ጠቁመው፥ መጽሐፍቱን ለማሳተምም በዞን አስተዳደሮች በኩል የጨረታ ሂደት የተጀመረ መሆኑን አስረድተዋል።
መስከረም 3 ቀን 2016 የመማር ማስተማር ስራ እንደሚጀመር ጠቅሰው፥ በትምህርት ዘመኑ የመማሪያና ማስተማሪያ መጽሐፍት በወቅቱ ለተማሪዎች እንዲደርሱ እየተሠራ መሆኑን ነው የተናገሩት።
በዮሐንስ ደርበው
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!