አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 9፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲዩትበስፔስ ሳይንስና ጆኦስፓሻል ዘርፍ ተሰጥኦ ላላቸው ታዳጊዎች በቡራዩ የልዩ ተሰጥኦ ማበልጸጊያ ማእከል ስልጠና በመሰጠት ላይ ይገኛል።
የስልጠናውን አጀማመርና ሂደት የጎበኙት የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አብዲሳ ይልማ፥ ስልጠናው ታዳጊዎች ያላቸውን ተሰጥኦ በማሳደግ ኢትዮጵያ በዘርፉ የምትፈልገውን የሰው ሃይል ለማዘጋጀና በዘርፉ በሀገር እቀፍ ደረጃ በሚደረገው እንቅስቃሴ ታዳጊዎች አስተዋጽኦ እንዲኖራቸው ያለመ ነው ብለዋል።
የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ጂኦስፖሻል ኢንስቲትዩት ኢትዮ-ስፔስ ኪድስ ክበብ በማቋቋም በዘርፉ ልዩ ተሰጥኦ ያላቸው ታዳጊዎችን በመመልመል ባለፉት ሁለት ዓመታት በክረምት ሲያሰለጥን ቆይቷል።
ዘንድሮም ፕሮግራሙን በአዲስ መልክ በጀማሪ መካከለኛና ከፍተኛ በሚል ሦስት ደረጃዎች በማደራጀት ስልጠና መስጠት መጀመሩም ነው የተገለጸው።
በከፍተኛ ደረጃ በሚሰጠው ስልጠና ተሰጥኦዎቻቸውን ወደ ተጨባጭ ምርትና አገልግሎት በመቀየር ሀገርንና ማህበረሰብን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ፕሮጀክቶች የሚሰሩበት እንደሚሆን የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ይሽሩን አለማየሁ(ዶ/ር) ተናግረዋል።
ኢንስቲትዩቱ በአዋጅ በተሰጠው ስልጣን መሰረት በስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ዘርፍ የስልጠንና የማማከር አገልግሎት እንደሚሰጥ ከኢንስቲትዩቱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!